TRADUZIONE AMARICA - African Academy
Traduzione dei significati del Nobile Corano
Tradotta da Muhammad Zain Zahreddin, edita dalla African Academy
وَٱلشَّمۡسِ وَضُحَىٰهَا
1. በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)
وَٱلۡقَمَرِ إِذَا تَلَىٰهَا
2. በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤
وَٱلنَّهَارِ إِذَا جَلَّىٰهَا
3. በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤
وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰهَا
4. በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤
وَٱلسَّمَآءِ وَمَا بَنَىٰهَا
5. በሰማይ እና በገነባትም፤
وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا طَحَىٰهَا
6. በምድር እና በዘረጋትም፤
وَنَفۡسٖ وَمَا سَوَّىٰهَا
7. በነፍስም ባስተካከላትም
فَأَلۡهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقۡوَىٰهَا
8. አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም በአላህ እምላለሁ)።
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن زَكَّىٰهَا
9. (ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።
وَقَدۡ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا
10. በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)::
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ بِطَغۡوَىٰهَآ
11. ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤
إِذِ ٱنۢبَعَثَ أَشۡقَىٰهَا
12. ጠማማዋ በተነሳ ጊዜ።
فَقَالَ لَهُمۡ رَسُولُ ٱللَّهِ نَاقَةَ ٱللَّهِ وَسُقۡيَٰهَا
13. ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው::
فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمۡدَمَ عَلَيۡهِمۡ رَبُّهُم بِذَنۢبِهِمۡ فَسَوَّىٰهَا
14. እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም::
وَلَا يَخَافُ عُقۡبَٰهَا
15. (የምታስተካክለውን) ፍፃሜዋንም አይፈራም።
share_via