阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。
《古兰经》含义翻译
由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。
عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ
1. ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፤
أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ
2. ዓይነስውሩ ወደ እርሱ ስለመጣ።
وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምን ያሳውቅሃል? ምን አልባትም (ይህ አይነስውር ሰው ካንተ በሚሰማው ምክር ከኃጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል::
أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ
4. ወይም ሊገሰጽና ግሳጼይቱም ልትጠቅመው ይከጀላል::
أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ
5. ያ! ከአላህ የተብቃቃውን ሰውማ፤
فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ
6. አንተ ለእርሱ ትዘጋጃለህ።
وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ
7. ባይጥራራ (ባያምን)፤ ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትሆን፤
وَأَمَّا مَن جَآءَكَ يَسۡعَىٰ
8. ያ! እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤
وَهُوَ يَخۡشَىٰ
9. እርሱ አላህን የሚፈራ ሲሆን፤
فَأَنتَ عَنۡهُ تَلَهَّىٰ
10. አንተ ከእርሱ ትዘናጋለህ::
كَلَّآ إِنَّهَا تَذۡكِرَةٞ
11. ተከልከል፤ (ቁርኣን) ማስገንዘቢያ ነው::
فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ
12. የፈለገ ሰው ሁሉ (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል::
فِي صُحُفٖ مُّكَرَّمَةٖ
13. በተከበሩት ጹሑፎች ውስጥ ነው::
مَّرۡفُوعَةٖ مُّطَهَّرَةِۭ
14. ከፍ በተደረገች፤ ንጹህም በተደረገች (ጹሑፍ ውስጥ ነው)።
بِأَيۡدِي سَفَرَةٖ
15. በጸሐፊዎች መላዕክት እጆች (ንጹህ የተደረገ)::
كِرَامِۭ بَرَرَةٖ
16. የተከበሩና ታዛዦች በሆኑት ጸሐፊዎች (እጆች)፤
قُتِلَ ٱلۡإِنسَٰنُ مَآ أَكۡفَرَهُۥ
17. ሰው ተረገመ። ምን ከሓዲ አደረገው?
مِنۡ أَيِّ شَيۡءٍ خَلَقَهُۥ
18. (ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው?
مِن نُّطۡفَةٍ خَلَقَهُۥ فَقَدَّرَهُۥ
19. (አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነዉም::
ثُمَّ ٱلسَّبِيلَ يَسَّرَهُۥ
20. ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው::
ثُمَّ أَمَاتَهُۥ فَأَقۡبَرَهُۥ
21. ከዚያም ገደለው:: እንዲቀበርም አደረገው፤
ثُمَّ إِذَا شَآءَ أَنشَرَهُۥ
22. ከዚያ ማንሳቱን በፈለገ ጊዜ ያስነሳዋል::
كَلَّا لَمَّا يَقۡضِ مَآ أَمَرَهُۥ
23. በእውነት ያንን ጌታው ያዘዘውን ገና አልፈጸመም::
فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ إِلَىٰ طَعَامِهِۦٓ
24. ሰው ወደ ምግቡ ይመልከት፤
أَنَّا صَبَبۡنَا ٱلۡمَآءَ صَبّٗا
25. እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤
ثُمَّ شَقَقۡنَا ٱلۡأَرۡضَ شَقّٗا
26. ከዚያ ምድርን በደካማ ቡቃያ መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤
فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا حَبّٗا
27. በውስጧም እህልን ያበቀልን
وَعِنَبٗا وَقَضۡبٗا
28. ወይንም እርጥብ ሳርንም፤
وَزَيۡتُونٗا وَنَخۡلٗا
29. የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤
وَحَدَآئِقَ غُلۡبٗا
30. ጭፍቆች አትክልቶችንም፤
وَفَٰكِهَةٗ وَأَبّٗا
31. ፍራፍሬንና፤ ገለባንም (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)።
مَّتَٰعٗا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ
32. ለእናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)::
فَإِذَا جَآءَتِ ٱلصَّآخَّةُ
33. አደንቋሪይቱ (መከራ) በመጣች ጊዜ፤
يَوۡمَ يَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِيهِ
34. ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤
وَأُمِّهِۦ وَأَبِيهِ
35. ከእናቱም፤ ከአባቱም፤ (በሚሸሽበት ቀን)
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَبَنِيهِ
36. ከሚስቱና ከልጁም፤ (በሚሸሽበት ቀን)
لِكُلِّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ يَوۡمَئِذٖ شَأۡنٞ يُغۡنِيهِ
37. ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን ከሌላው የሚያብቃቃው ሁኔታ አለው::
وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ مُّسۡفِرَةٞ
38. ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች፤
ضَاحِكَةٞ مُّسۡتَبۡشِرَةٞ
39. ሳቂዎችና ተደሳቾች ናቸው::
وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذٍ عَلَيۡهَا غَبَرَةٞ
40. ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትብያ አለባቸው።
تَرۡهَقُهَا قَتَرَةٌ
41. ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَفَرَةُ ٱلۡفَجَرَةُ
42. እነዚያ እነርሱ በአላህ ከሓዲያን እና በትዕዛዙ ላይ አመጸኞቹ ናቸው።
share_via