阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。
《古兰经》含义翻译
由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنشَقَّتۡ
1. ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤
وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ
2. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
وَإِذَا ٱلۡأَرۡضُ مُدَّتۡ
3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
وَأَلۡقَتۡ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتۡ
4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤
وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ
5. ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (ልትስማ) ተገባትም፤
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدۡحٗا فَمُلَٰقِيهِ
6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን በሞት እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ።
فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ
7. ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጅ የተሰጠውማ
فَسَوۡفَ يُحَاسَبُ حِسَابٗا يَسِيرٗا
8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል።
وَيَنقَلِبُ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورٗا
9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል::
وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ وَرَآءَ ظَهۡرِهِۦ
10. ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን
فَسَوۡفَ يَدۡعُواْ ثُبُورٗا
11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል::
وَيَصۡلَىٰ سَعِيرًا
12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል::
إِنَّهُۥ كَانَ فِيٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا
13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤
إِنَّهُۥ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ
14. እርሱም ወደ አላህ እንደማይመለስ አሰበ።
بَلَىٰٓۚ إِنَّ رَبَّهُۥ كَانَ بِهِۦ بَصِيرٗا
15. አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (መመለስ) አዋቂ ነው።
فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلشَّفَقِ
16. ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ።
وَٱلَّيۡلِ وَمَا وَسَقَ
17. በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤
وَٱلۡقَمَرِ إِذَا ٱتَّسَقَ
18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)።
لَتَرۡكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٖ
19. ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን ትሸጋገራላችሁ።
فَمَا لَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)?
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقُرۡءَانُ لَا يَسۡجُدُونَۤ۩
21. በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው?
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ
22. በእርግጥ እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ።
وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُوعُونَ
23. አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونِۭ
25.እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።
share_via