Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija
Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.
لَآ أُقۡسِمُ بِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ
1. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በትንሳኤ ቀን እምላለሁ::
وَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ
2. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ::
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجۡمَعَ عِظَامَهُۥ
3. (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ።) ሰው አጥንቶችን ለመሰብሰባችን ይጠራጠራልን?
بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُۥ
4. እንዴታ ጣቶቹንም ፊት እንደነበሩት በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)።
بَلۡ يُرِيدُ ٱلۡإِنسَٰنُ لِيَفۡجُرَ أَمَامَهُۥ
5. ይልቁን ሰው በፊቱ ባለ ነገር በትንሳኤ ቀን ሊያስተባብል ይፈልጋል::
يَسۡـَٔلُ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلۡقِيَٰمَةِ
6. «የትንሳኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል።
فَإِذَا بَرِقَ ٱلۡبَصَرُ
7. ዓይንም በዋለለ ጊዜ::
وَخَسَفَ ٱلۡقَمَرُ
8. ጨረቃም በጨለመ ጊዜ::
وَجُمِعَ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ
9. ጸሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤
يَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذٍ أَيۡنَ ٱلۡمَفَرُّ
10. ሰው በዚያን ቀን «መሸሻው የት ነው?» ይላል።
كَلَّا لَا وَزَرَ
11. «ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም።
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمُسۡتَقَرُّ
12. በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።» ይባላል።
يُنَبَّؤُاْ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذِۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ
13. ሰው በዚያን ቀን ያስቀደመውም ያስቆየውም ሁሉ ይነገረዋል።
بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٞ
14. በእርግጥ ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው::
وَلَوۡ أَلۡقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ
15. ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣ እንኳን (አይሰማም)።
لَا تُحَرِّكۡ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعۡجَلَ بِهِۦٓ
16. በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ብለህ ምላስህን አታላውስ::
إِنَّ عَلَيۡنَا جَمۡعَهُۥ وَقُرۡءَانَهُۥ
17. በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማስነበቡ በኛ ላይ ነውና::
فَإِذَا قَرَأۡنَٰهُ فَٱتَّبِعۡ قُرۡءَانَهُۥ
18. ባነበብነው ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል።
ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا بَيَانَهُۥ
19. ከዚያም (ላንተ) ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው።
كَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጣደፍ ተከልከል፤ ይልቁንም (ሰዎች ስትባሉ) ፈጣኒቱን ዓለም ትወዳላችሁ::
وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ
21. የመጨረሻይቱን ዓለም (ግን) ትተዋላችሁ።
وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاضِرَةٌ
22. (የተወሰኑ) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው።
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٞ
23. ወደ ጌታቸው ተመልካቾችም ናቸው::
وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٞ
24. (ሌሎች) ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን አጨፍጋጊዎች ናቸው።
تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٞ
25. በእነርሱም ላይ አደጋ እንደሚሰራባቸው ያረጋገጣሉ::
كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ
26. (ሙስሊሞች አስተውሉ።) (ነፍስ) ወደ ጉሮሮ በደረሰች፤
وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٖ
27. «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፤
وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ
28. (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ፤
وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ
29. ባትም ከባት በተጣበቀች ጊዜ፤
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ
30. በዚያ ቀን መነዳት ወደ ጌታህ (ፍርድ) ብቻ ነው።
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ
31. እናም (ከሀዲው) አላመነምም፤ አልሰገደምም።
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
32. ግን በአላህ አስተባበለ፤ ከእምነት ዞረም::
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ
33. ከዚያም እየተንጎማለለ ወደ ቤተሰቡ ሄደ።
أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ
34. (የምትጠላውን ነገር) ላንተው ይሁን፤ ላንተ ተገቢህም ነው።
ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ
35. ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ላንተ የተገባህም ነው።
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى
36. ሰው እንደፈለገ እንዲኖር ልቅ ሆኖ የሚተው ይመስለዋልን?
أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةٗ مِّن مَّنِيّٖ يُمۡنَىٰ
37. የሚፈስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةٗ فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
38. ከዚያ የረጋ ደም ሆነ:: ከዚያ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠረው፤ አስተካከለዉም::
فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ
39. ከእርሱም ሁለት ዓይነቶች ወንድና ሴትን አደረገ።
أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ
40. (ታዲያ) ይህ ሀያል (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?
مشاركة عبر