Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija
Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.
وَٱلۡمُرۡسَلَٰتِ عُرۡفٗا
1. ተከታታይ ሆነው በተላኩት ፤ (እምላለሁ)፡፡
فَٱلۡعَٰصِفَٰتِ عَصۡفٗا
2. በኃይል መንፈስን ነፋሾች በሆኑትም (ንፋሶች)፤
وَٱلنَّٰشِرَٰتِ نَشۡرٗا
3. መበተንን በታኝ በሆኑትም (ንፋሶች)፤
فَٱلۡفَٰرِقَٰتِ فَرۡقٗا
4. መለየትን ለይዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤
فَٱلۡمُلۡقِيَٰتِ ذِكۡرًا
5. መገሰጫን (ወደ ነብያት ጣይዎች) አምጪዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤
عُذۡرًا أَوۡ نُذۡرًا
6. ማሳበቢያን ለማስወገድ ወይም ለማስጠንቀቅ፤
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَوَٰقِعٞ
7. ያ! የምትስፈራሩበት (ትንሳኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው ብየ እምላለሁ::
فَإِذَا ٱلنُّجُومُ طُمِسَتۡ
8. ከዋክብትም (ብርሃኗ) በታበሰች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ فُرِجَتۡ
9. ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ نُسِفَتۡ
10. ጋራዎችም በተንኮታኮቱ ጊዜ::
وَإِذَا ٱلرُّسُلُ أُقِّتَتۡ
11. መልዕክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፤
لِأَيِّ يَوۡمٍ أُجِّلَتۡ
12. ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ የሚባል ሲሆን፤
لِيَوۡمِ ٱلۡفَصۡلِ
13. ለዚያ ለመለያው ቀን ተቀጠሩ በተባለ ጊዜ (በፍጡሮች መካከል በትክክል ይፈርዳል)፤
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመለያው ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
15. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
أَلَمۡ نُهۡلِكِ ٱلۡأَوَّلِينَ
16. የፊተኞቹን (ህዝቦች) አላጠፋንምን?
ثُمَّ نُتۡبِعُهُمُ ٱلۡأٓخِرِينَ
17. ከዚያ ኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን::
كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ
18. በአመጸኞች ሁሉ ላይ ልክ እንደዚሁ (ያለ) እንሰራለን።
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
19. ለአስተባባዩች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
أَلَمۡ نَخۡلُقكُّم مِّن مَّآءٖ مَّهِينٖ
20. (ሰዎች ሆይ!) ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?
فَجَعَلۡنَٰهُ فِي قَرَارٖ مَّكِينٍ
21. በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በእናቶች ማህጸን) ውስጥ አደረግነው::
إِلَىٰ قَدَرٖ مَّعۡلُومٖ
22. እስከታወቀ ጊዜ ድረስ::
فَقَدَرۡنَا فَنِعۡمَ ٱلۡقَٰدِرُونَ
23.መጠንነዉም ምን ያማርንም መጣኞች ነን::
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
24. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።
أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ كِفَاتًا
25. (ሰዎች ሆይ!) ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን::
أَحۡيَآءٗ وَأَمۡوَٰتٗا
26. ህያው ሆናችሁም ሙታን ሆናችሁም።
وَجَعَلۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ شَٰمِخَٰتٖ وَأَسۡقَيۡنَٰكُم مَّآءٗ فُرَاتٗا
27. በውስጧም ከፍተኛዎችን (ትላልቅ) ተራራዎች አደረግን፤ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ::
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
28. ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላችሁ::
ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ مَا كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
29. «ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት ቅጣት ሂዱ።
ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ ظِلّٖ ذِي ثَلَٰثِ شُعَبٖ
30. ባለ ሶስት ቅርንጫፎች ወደ ሆነው ጥላ ሂዱ።» (ይባላሉም)
لَّا ظَلِيلٖ وَلَا يُغۡنِي مِنَ ٱللَّهَبِ
31. ጥላም ያልሆነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ሆነው (ሂዱ)::
إِنَّهَا تَرۡمِي بِشَرَرٖ كَٱلۡقَصۡرِ
32. እርሷ እንደ ታላላቅ ህንፃ የሆኑን ቃንቄዎች (የእሳት ፍንጣሪዎች) ትወረውራለች::
كَأَنَّهُۥ جِمَٰلَتٞ صُفۡرٞ
33. (ቃንቄዉም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል።
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
34. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
هَٰذَا يَوۡمُ لَا يَنطِقُونَ
35. ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው።
وَلَا يُؤۡذَنُ لَهُمۡ فَيَعۡتَذِرُونَ
36. ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ አይፈቀድላቸዉም::
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
37. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮውላቸው።
هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِۖ جَمَعۡنَٰكُمۡ وَٱلۡأَوَّلِينَ
38. ይህ የመለያው ቀን ነው። እናንተንም የፊተኞችንም ሰበሰብናችሁ።
فَإِن كَانَ لَكُمۡ كَيۡدٞ فَكِيدُونِ
39. ለእናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ።
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
40. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي ظِلَٰلٖ وَعُيُونٖ
41. ጥንቅቆች በጥላዎችና በምንጮች፤ውስጥ ናቸው፡፡
وَفَوَٰكِهَ مِمَّا يَشۡتَهُونَ
42. በሚፈልጉትም የፍራፍሬ (አይነቶች) ውስጥ ናቸው።
كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
43. «ትሰሩትም በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ሆናችሁ ብሉ፤ ጠጡም» ይባላሉ፤
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
44. እኛ መልካም ሰሪዎችን (ሁሉ) እንደዚሁ እንመነዳለን፤
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
45. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
كُلُواْ وَتَمَتَّعُواْ قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجۡرِمُونَ
46. አስትባባዮች ሆይ! ብሉ ጥቂትንም ጊዜ ተጠቀሙ እናንተ አመጸኞች ናችሁና::
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
47. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱرۡكَعُواْ لَا يَرۡكَعُونَ
48. ለእነርሱ «ስገዱ» በተባሉም ጊዜ አይሰግዱም።
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
49. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።
فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَهُۥ يُؤۡمِنُونَ
50. ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
مشاركة عبر