Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/sr/amharic_zain

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ ٱتَّقِ ٱللَّهَ وَلَا تُطِعِ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقِينَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمٗا

1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህን ፍራ:: ከሓዲያንንና አስመሳዮችንም አትታዘዝ:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህን ፍራ:: ከሓዲያንንና አስመሳዮችንም አትታዘዝ:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

وَٱتَّبِعۡ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٗا

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም ወደ አንተ የሚወረደውን ብቻ ተከተል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም ወደ አንተ የሚወረደውን ብቻ ተከተል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلٗا

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ተመካ:: መመኪያነትም በአላህ ብቻ በቃ።

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ተመካ:: መመኪያነትም በአላህ ብቻ በቃ።

مَّا جَعَلَ ٱللَّهُ لِرَجُلٖ مِّن قَلۡبَيۡنِ فِي جَوۡفِهِۦۚ وَمَا جَعَلَ أَزۡوَٰجَكُمُ ٱلَّٰٓـِٔي تُظَٰهِرُونَ مِنۡهُنَّ أُمَّهَٰتِكُمۡۚ وَمَا جَعَلَ أَدۡعِيَآءَكُمۡ أَبۡنَآءَكُمۡۚ ذَٰلِكُمۡ قَوۡلُكُم بِأَفۡوَٰهِكُمۡۖ وَٱللَّهُ يَقُولُ ٱلۡحَقَّ وَهُوَ يَهۡدِي ٱلسَّبِيلَ

4. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም:: እነዚያን «እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይሁኑብን» የምትሏቸውን ሚስቶቻችሁንም እናቶቻችሁ አላደረገም:: ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም:: ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ቃላችሁ ብቻ ነው:: አላህ እውነትን ይናገራል:: ትክክለኛውን መንገድም ይመራል::

ٱدۡعُوهُمۡ لِأٓبَآئِهِمۡ هُوَ أَقۡسَطُ عِندَ ٱللَّهِۚ فَإِن لَّمۡ تَعۡلَمُوٓاْ ءَابَآءَهُمۡ فَإِخۡوَٰنُكُمۡ فِي ٱلدِّينِ وَمَوَٰلِيكُمۡۚ وَلَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٞ فِيمَآ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمًا

5. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውን) በአባቶቻቸው ስም በማስጠጋት ጥሯቸው:: እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛው መንገድ ነውና:: አባቶቻቸውን ባታውቁም በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው:: በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ልቦቻችሁ አውቀው በሰራችሁት ስህተት ግን ኃጢአት አለባችሁ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

ٱلنَّبِيُّ أَوۡلَىٰ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ مِنۡ أَنفُسِهِمۡۖ وَأَزۡوَٰجُهُۥٓ أُمَّهَٰتُهُمۡۗ وَأُوْلُواْ ٱلۡأَرۡحَامِ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلَىٰ بِبَعۡضٖ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُهَٰجِرِينَ إِلَّآ أَن تَفۡعَلُوٓاْ إِلَىٰٓ أَوۡلِيَآئِكُم مَّعۡرُوفٗاۚ كَانَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَسۡطُورٗا

6. ነብዩ (ሙሐመድ) ለአማኞች ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ቀራቢ ነው:: ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው:: የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ (ለውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከአማኞችና ከስደተኞች ይልቅ የተገባቸው ናቸው:: ለወዳጆቻችሁ በኑዛዜ መልካም ስራን ብትሰሩ ግን ይፈቀዳል:: ይህ በአላህ መጽሐፉ ውስጥ ቀድሞውኑ የተመዘገበ ነው::

وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِيثَٰقَهُمۡ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٖ وَإِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ٱبۡنِ مَرۡيَمَۖ وَأَخَذۡنَا مِنۡهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከነብዮችም ካንተም፤ ከኑህም፤ ከኢብራሂምም፤ ከሙሳም፤ ከመርየም ልጅ ዒሳም የጠበቀ ቃልኪዳናቸውን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን::

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከነብዮችም ካንተም፤ ከኑህም፤ ከኢብራሂምም፤ ከሙሳም፤ ከመርየም ልጅ ዒሳም የጠበቀ ቃልኪዳናቸውን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን::

لِّيَسۡـَٔلَ ٱلصَّٰدِقِينَ عَن صِدۡقِهِمۡۚ وَأَعَدَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابًا أَلِيمٗا

8. አላህ እውነተኞችን ከእውነታቸው ሊጠይቃቸው (ይህንን ሰራ):: ለከሓዲያንም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ::

8. አላህ እውነተኞችን ከእውነታቸው ሊጠይቃቸው (ይህንን ሰራ):: ለከሓዲያንም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ جَآءَتۡكُمۡ جُنُودٞ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا وَجُنُودٗا لَّمۡ تَرَوۡهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرًا

9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣባችሁና በእነርሱ ላይ ንፋስንና በአይናችሁ ያላያችሁትን ሰራዊት በላክን ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህም የምትሰሩትን ተመልካች ነው።

9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣባችሁና በእነርሱ ላይ ንፋስንና በአይናችሁ ያላያችሁትን ሰራዊት በላክን ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህም የምትሰሩትን ተመልካች ነው።

إِذۡ جَآءُوكُم مِّن فَوۡقِكُمۡ وَمِنۡ أَسۡفَلَ مِنكُمۡ وَإِذۡ زَاغَتِ ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَبَلَغَتِ ٱلۡقُلُوبُ ٱلۡحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِٱللَّهِ ٱلظُّنُونَا۠

10. ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ፤ ዓይኖችም በቃበዙ፤ ልቦችም ወደ ላንቃዎች በደረሱና በአላህም መጥፎ ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ (አስታውሱ)::

10. ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ፤ ዓይኖችም በቃበዙ፤ ልቦችም ወደ ላንቃዎች በደረሱና በአላህም መጥፎ ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ (አስታውሱ)::

هُنَالِكَ ٱبۡتُلِيَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَزُلۡزِلُواْ زِلۡزَالٗا شَدِيدٗا

11. እዚያ ዘንድ አማኞች ተሞከሩ:: ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ::

11. እዚያ ዘንድ አማኞች ተሞከሩ:: ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ::

وَإِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ مَّا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ إِلَّا غُرُورٗا

12. መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ «አላህና መልዕክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም።» በሚሉም ጊዜ ያደረገላችሁን ውለታ አስታውሱ::

12. መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ «አላህና መልዕክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም።» በሚሉም ጊዜ ያደረገላችሁን ውለታ አስታውሱ::

وَإِذۡ قَالَت طَّآئِفَةٞ مِّنۡهُمۡ يَٰٓأَهۡلَ يَثۡرِبَ لَا مُقَامَ لَكُمۡ فَٱرۡجِعُواْۚ وَيَسۡتَـٔۡذِنُ فَرِيقٞ مِّنۡهُمُ ٱلنَّبِيَّ يَقُولُونَ إِنَّ بُيُوتَنَا عَوۡرَةٞ وَمَا هِيَ بِعَوۡرَةٍۖ إِن يُرِيدُونَ إِلَّا فِرَارٗا

13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም የሆነ ቡድን «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከእነርሱም መካከል ከፊሎቹ ነውረኛ ሳይሆኑ «ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው።» በማለት ነብዩን ከጦሩ ለመመለስ ፈቃድን ይጠይቃሉ:: መሸሽን እንጂ ሌላን አይፈልጉም::

13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም የሆነ ቡድን «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከእነርሱም መካከል ከፊሎቹ ነውረኛ ሳይሆኑ «ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው።» በማለት ነብዩን ከጦሩ ለመመለስ ፈቃድን ይጠይቃሉ:: መሸሽን እንጂ ሌላን አይፈልጉም::

وَلَوۡ دُخِلَتۡ عَلَيۡهِم مِّنۡ أَقۡطَارِهَا ثُمَّ سُئِلُواْ ٱلۡفِتۡنَةَ لَأٓتَوۡهَا وَمَا تَلَبَّثُواْ بِهَآ إِلَّا يَسِيرٗا

14. በእርሱም ላይ በቤቶቻቸው ከየቀበሌዋ ከጠላት በተገባባትና ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በፍጥነት በሰሯት ነበር ፡፡ በእሷ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር ፡፡

14. በእርሱም ላይ በቤቶቻቸው ከየቀበሌዋ ከጠላት በተገባባትና ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በፍጥነት በሰሯት ነበር ፡፡ በእሷ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር ፡፡

وَلَقَدۡ كَانُواْ عَٰهَدُواْ ٱللَّهَ مِن قَبۡلُ لَا يُوَلُّونَ ٱلۡأَدۡبَٰرَۚ وَكَانَ عَهۡدُ ٱللَّهِ مَسۡـُٔولٗا

15. ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያም በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የገቡ ነበሩ:: የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ትልቅ ሀላፊነት ነው::

15. ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያም በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የገቡ ነበሩ:: የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ትልቅ ሀላፊነት ነው::

قُل لَّن يَنفَعَكُمُ ٱلۡفِرَارُ إِن فَرَرۡتُم مِّنَ ٱلۡمَوۡتِ أَوِ ٱلۡقَتۡلِ وَإِذٗا لَّا تُمَتَّعُونَ إِلَّا قَلِيلٗا

16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም:: ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም።» በላቸው።

16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም:: ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም።» በላቸው።

قُلۡ مَن ذَا ٱلَّذِي يَعۡصِمُكُم مِّنَ ٱللَّهِ إِنۡ أَرَادَ بِكُمۡ سُوٓءًا أَوۡ أَرَادَ بِكُمۡ رَحۡمَةٗۚ وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሙስሊምቸ ሆይ!) «አላህ በእናንተ ላይ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማን ነው? ወይም ለእናንተ እዝነትን ቢፈልግ ክፉ የሚያመጣባችሁ ማን ነው?» በላቸው። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ሆነ ረዳት አያገኙም።

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሙስሊምቸ ሆይ!) «አላህ በእናንተ ላይ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማን ነው? ወይም ለእናንተ እዝነትን ቢፈልግ ክፉ የሚያመጣባችሁ ማን ነው?» በላቸው። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ሆነ ረዳት አያገኙም።

۞ قَدۡ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ ٱلۡمُعَوِّقِينَ مِنكُمۡ وَٱلۡقَآئِلِينَ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ هَلُمَّ إِلَيۡنَاۖ وَلَا يَأۡتُونَ ٱلۡبَأۡسَ إِلَّا قَلِيلًا

18. ከናንተ ውስጥ የሚያደናቅፉትን ለወንድሞቻቸዉም «ወደ እኛ ኑ» የሚሉትን፤ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል::

18. ከናንተ ውስጥ የሚያደናቅፉትን ለወንድሞቻቸዉም «ወደ እኛ ኑ» የሚሉትን፤ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል::

أَشِحَّةً عَلَيۡكُمۡۖ فَإِذَا جَآءَ ٱلۡخَوۡفُ رَأَيۡتَهُمۡ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ تَدُورُ أَعۡيُنُهُمۡ كَٱلَّذِي يُغۡشَىٰ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡمَوۡتِۖ فَإِذَا ذَهَبَ ٱلۡخَوۡفُ سَلَقُوكُم بِأَلۡسِنَةٍ حِدَادٍ أَشِحَّةً عَلَى ٱلۡخَيۡرِۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يُؤۡمِنُواْ فَأَحۡبَطَ ٱللَّهُ أَعۡمَٰلَهُمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا

19. (አማኞች ሆይ!) በእናንተ ላይ እርዳታን የነፈጉ ሆነው እንጂ የማይመጡትን፤ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት መከራ በእርሱ ላይ የሚሸፍን አደጋ እንደ ወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትንከራተት ሆና ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ሽብሩም በሄደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ሆነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል:: እነዚያ አላመኑም:: ስለዚህ አላህ ስራዎቻቸውን አበላሸ:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።

يَحۡسَبُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ لَمۡ يَذۡهَبُواْۖ وَإِن يَأۡتِ ٱلۡأَحۡزَابُ يَوَدُّواْ لَوۡ أَنَّهُم بَادُونَ فِي ٱلۡأَعۡرَابِ يَسۡـَٔلُونَ عَنۡ أَنۢبَآئِكُمۡۖ وَلَوۡ كَانُواْ فِيكُم مَّا قَٰتَلُوٓاْ إِلَّا قَلِيلٗا

20. (መናፍቆች) አህዛብን አልሄዱም ብለው ያስባሉ አህዛቦችም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር የራቁ ሊሆኑ ይመኛሉ:: (ከዚያም) ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ:: በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር::

20. (መናፍቆች) አህዛብን አልሄዱም ብለው ያስባሉ አህዛቦችም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር የራቁ ሊሆኑ ይመኛሉ:: (ከዚያም) ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ:: በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር::

لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِي رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ لِّمَن كَانَ يَرۡجُواْ ٱللَّهَ وَٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا

21. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው ሁሉ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ::

21. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው ሁሉ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ::

وَلَمَّا رَءَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ قَالُواْ هَٰذَا مَا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَصَدَقَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥۚ وَمَا زَادَهُمۡ إِلَّآ إِيمَٰنٗا وَتَسۡلِيمٗا

22. አማኞችም አህዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልዕክተኛው የቀጠሩን ነው:: አላህና መልዕክተኛዉም እውነትን ተናገሩ።» አሉ:: ይህ እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸዉም::

22. አማኞችም አህዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልዕክተኛው የቀጠሩን ነው:: አላህና መልዕክተኛዉም እውነትን ተናገሩ።» አሉ:: ይህ እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸዉም::

مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ رِجَالٞ صَدَقُواْ مَا عَٰهَدُواْ ٱللَّهَ عَلَيۡهِۖ فَمِنۡهُم مَّن قَضَىٰ نَحۡبَهُۥ وَمِنۡهُم مَّن يَنتَظِرُۖ وَمَا بَدَّلُواْ تَبۡدِيلٗا

23. ከአማኞች መካከል በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ። ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ ለሃይማኖቱ የተገደለም አለ:: ከእነርሱም መካከል ገና የሚጠባበቅ አለ:: የገቡትን ቃል መለወጥንም አለወጡም::

23. ከአማኞች መካከል በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ። ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ ለሃይማኖቱ የተገደለም አለ:: ከእነርሱም መካከል ገና የሚጠባበቅ አለ:: የገቡትን ቃል መለወጥንም አለወጡም::

لِّيَجۡزِيَ ٱللَّهُ ٱلصَّٰدِقِينَ بِصِدۡقِهِمۡ وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ إِن شَآءَ أَوۡ يَتُوبَ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

24. አላህ እውነተኞችን በእውነተኛነታቸው ሊመነዳ፤ አስመሳዮችንም ቢፈልግ ሊቀጣ ወይም ቢመለሱ በእነርሱ ላይ ጸጸታቸቸውን ሊቀበል ይህን አደረገ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

24. አላህ እውነተኞችን በእውነተኛነታቸው ሊመነዳ፤ አስመሳዮችንም ቢፈልግ ሊቀጣ ወይም ቢመለሱ በእነርሱ ላይ ጸጸታቸቸውን ሊቀበል ይህን አደረገ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

وَرَدَّ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِغَيۡظِهِمۡ لَمۡ يَنَالُواْ خَيۡرٗاۚ وَكَفَى ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلۡقِتَالَۚ وَكَانَ ٱللَّهُ قَوِيًّا عَزِيزٗا

25. እነዚያንም በአላህ የካዱትን በቁጭታቸው የተሞሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ መለሳቸው:: አማኞቹንም አላህ መጋደልን በቃቸው:: አላህም ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::

25. እነዚያንም በአላህ የካዱትን በቁጭታቸው የተሞሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ መለሳቸው:: አማኞቹንም አላህ መጋደልን በቃቸው:: አላህም ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::

وَأَنزَلَ ٱلَّذِينَ ظَٰهَرُوهُم مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مِن صَيَاصِيهِمۡ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعۡبَ فَرِيقٗا تَقۡتُلُونَ وَتَأۡسِرُونَ فَرِيقٗا

26. እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች አህዛቦችን የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው። ከፊሉን ትገድላላችሁ፤ ከፊሉንም ትማርካላችሁ::

26. እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች አህዛቦችን የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው። ከፊሉን ትገድላላችሁ፤ ከፊሉንም ትማርካላችሁ::

وَأَوۡرَثَكُمۡ أَرۡضَهُمۡ وَدِيَٰرَهُمۡ وَأَمۡوَٰلَهُمۡ وَأَرۡضٗا لَّمۡ تَطَـُٔوهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٗا

27. ምድራቸውንም ቤቶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

27. ምድራቸውንም ቤቶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ قُل لِّأَزۡوَٰجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدۡنَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيۡنَ أُمَتِّعۡكُنَّ وَأُسَرِّحۡكُنَّ سَرَاحٗا جَمِيلٗا

28. አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው: «ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ:: አጣቅማችኋለሁና መልካምንም መፍታት እፈታችኋለሁና::

28. አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው: «ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ:: አጣቅማችኋለሁና መልካምንም መፍታት እፈታችኋለሁና::

وَإِن كُنتُنَّ تُرِدۡنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَ فَإِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلۡمُحۡسِنَٰتِ مِنكُنَّ أَجۡرًا عَظِيمٗا

29. «አላህንና መልዕክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ከሆናችሁ እነሆ አላህ ከናንተ ለመልካም ሰሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል።»

29. «አላህንና መልዕክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ከሆናችሁ እነሆ አላህ ከናንተ ለመልካም ሰሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል።»

يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِيِّ مَن يَأۡتِ مِنكُنَّ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖ يُضَٰعَفۡ لَهَا ٱلۡعَذَابُ ضِعۡفَيۡنِۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا

30. እናንተ የነብዩ ሚስቶች ሆይ! ከናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ስራ የምትሰራ ሴት ቅጣቷ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል:: ይህም በአላህ ዘንድ ገር ነው::

30. እናንተ የነብዩ ሚስቶች ሆይ! ከናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ስራ የምትሰራ ሴት ቅጣቷ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል:: ይህም በአላህ ዘንድ ገር ነው::

۞ وَمَن يَقۡنُتۡ مِنكُنَّ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتَعۡمَلۡ صَٰلِحٗا نُّؤۡتِهَآ أَجۡرَهَا مَرَّتَيۡنِ وَأَعۡتَدۡنَا لَهَا رِزۡقٗا كَرِيمٗا

31. ከናንተም መካከል ለአላህና ለመልዕክተኛው የምትታዘዝ መልካም ስራንም የምትሰራ ሴት ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን:: ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል።

31. ከናንተም መካከል ለአላህና ለመልዕክተኛው የምትታዘዝ መልካም ስራንም የምትሰራ ሴት ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን:: ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል።

يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِيِّ لَسۡتُنَّ كَأَحَدٖ مِّنَ ٱلنِّسَآءِ إِنِ ٱتَّقَيۡتُنَّۚ فَلَا تَخۡضَعۡنَ بِٱلۡقَوۡلِ فَيَطۡمَعَ ٱلَّذِي فِي قَلۡبِهِۦ مَرَضٞ وَقُلۡنَ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗا

32. እናንተ የነቢዩ ሚስቶች ሆይ! እንደ ማናቸዉም ሴቶች አይደላችሁም:: አላህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር እንኳን አትለስልሱም:: መልካምንም ንግግር ተናገሩ።

32. እናንተ የነቢዩ ሚስቶች ሆይ! እንደ ማናቸዉም ሴቶች አይደላችሁም:: አላህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር እንኳን አትለስልሱም:: መልካምንም ንግግር ተናገሩ።

وَقَرۡنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجۡنَ تَبَرُّجَ ٱلۡجَٰهِلِيَّةِ ٱلۡأُولَىٰۖ وَأَقِمۡنَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتِينَ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِعۡنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُذۡهِبَ عَنكُمُ ٱلرِّجۡسَ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِ وَيُطَهِّرَكُمۡ تَطۡهِيرٗا

33. በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ:: እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገላለጥም (በመጌጥ) አትገለጡ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ:: የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው::

33. በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ:: እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገላለጥም (በመጌጥ) አትገለጡ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ:: የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው::

وَٱذۡكُرۡنَ مَا يُتۡلَىٰ فِي بُيُوتِكُنَّ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ وَٱلۡحِكۡمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ لَطِيفًا خَبِيرًا

34. ከአላህ አናቅጽና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ:: አላህ እዝነቱ ረቂቅና ውስጠ አዋቂ ነውና::

34. ከአላህ አናቅጽና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ:: አላህ እዝነቱ ረቂቅና ውስጠ አዋቂ ነውና::

إِنَّ ٱلۡمُسۡلِمِينَ وَٱلۡمُسۡلِمَٰتِ وَٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ وَٱلۡقَٰنِتِينَ وَٱلۡقَٰنِتَٰتِ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلصَّٰدِقَٰتِ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰبِرَٰتِ وَٱلۡخَٰشِعِينَ وَٱلۡخَٰشِعَٰتِ وَٱلۡمُتَصَدِّقِينَ وَٱلۡمُتَصَدِّقَٰتِ وَٱلصَّٰٓئِمِينَ وَٱلصَّٰٓئِمَٰتِ وَٱلۡحَٰفِظِينَ فُرُوجَهُمۡ وَٱلۡحَٰفِظَٰتِ وَٱلذَّٰكِرِينَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱلذَّٰكِرَٰتِ أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُم مَّغۡفِرَةٗ وَأَجۡرًا عَظِيمٗا

35. ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፤ ምእምናንና ምዕመናትም፤ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፤ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፤ ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶችም፤ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶችም፤ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶችም፤ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶችም፤ ካልተፈቀደ ስራ ብልቶቻቸውን ጠባቂ ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፤ አላህን በብዙ አውሺ ወንዶችና አውሺ ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::

وَمَا كَانَ لِمُؤۡمِنٖ وَلَا مُؤۡمِنَةٍ إِذَا قَضَى ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَمۡرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ ٱلۡخِيَرَةُ مِنۡ أَمۡرِهِمۡۗ وَمَن يَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلٗا مُّبِينٗا

36. አላህና መልዕክተኛው በአንድ ነገር ላይ በወሰኑ ጊዜ ለምዕምናንና ለምዕመናት ከተነገራቸው ከመቀበል ዉጭ ምንም ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም:: የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ የጣሰ ሰው ሁሉ ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::

36. አላህና መልዕክተኛው በአንድ ነገር ላይ በወሰኑ ጊዜ ለምዕምናንና ለምዕመናት ከተነገራቸው ከመቀበል ዉጭ ምንም ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም:: የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ የጣሰ ሰው ሁሉ ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::

وَإِذۡ تَقُولُ لِلَّذِيٓ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ وَأَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِ أَمۡسِكۡ عَلَيۡكَ زَوۡجَكَ وَٱتَّقِ ٱللَّهَ وَتُخۡفِي فِي نَفۡسِكَ مَا ٱللَّهُ مُبۡدِيهِ وَتَخۡشَى ٱلنَّاسَ وَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخۡشَىٰهُۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيۡدٞ مِّنۡهَا وَطَرٗا زَوَّجۡنَٰكَهَا لِكَيۡ لَا يَكُونَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ حَرَجٞ فِيٓ أَزۡوَٰجِ أَدۡعِيَآئِهِمۡ إِذَا قَضَوۡاْ مِنۡهُنَّ وَطَرٗاۚ وَكَانَ أَمۡرُ ٱللَّهِ مَفۡعُولٗا

37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና አንተም (ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህን ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ያዝ:: አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ):: ዘይድም ከእርሷ ጉዳዩን በፈጸመ ጊዜ በምዕመኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጓቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይደርስባቸው እርሷን አጋባንህ (ዳርንህ):: የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው::

مَّا كَانَ عَلَى ٱلنَّبِيِّ مِنۡ حَرَجٖ فِيمَا فَرَضَ ٱللَّهُ لَهُۥۖ سُنَّةَ ٱللَّهِ فِي ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلُۚ وَكَانَ أَمۡرُ ٱللَّهِ قَدَرٗا مَّقۡدُورًا

38. በነብዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም:: በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት ነብያት አላህ ደነገገው። የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው::

38. በነብዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም:: በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት ነብያት አላህ ደነገገው። የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው::

ٱلَّذِينَ يُبَلِّغُونَ رِسَٰلَٰتِ ٱللَّهِ وَيَخۡشَوۡنَهُۥ وَلَا يَخۡشَوۡنَ أَحَدًا إِلَّا ٱللَّهَۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبٗا

39. ለእነዚያ የአላህን መልዕክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት ተደነገገ። ተቆጣጣሪነትም በአላህ በቃ::

39. ለእነዚያ የአላህን መልዕክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት ተደነገገ። ተቆጣጣሪነትም በአላህ በቃ::

مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٖ مِّن رِّجَالِكُمۡ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

40. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::

40. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ ذِكۡرٗا كَثِيرٗا

41. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት::

41. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት::

وَسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا

42. በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት::

42. በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት::

هُوَ ٱلَّذِي يُصَلِّي عَلَيۡكُمۡ وَمَلَٰٓئِكَتُهُۥ لِيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَكَانَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ رَحِيمٗا

43. እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው:: መላእክቶችም እንደዚሁ ምህረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው:: ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል):: ለትክክለኛ አማኞችም በጣም አዛኝ ነው::

43. እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው:: መላእክቶችም እንደዚሁ ምህረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው:: ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል):: ለትክክለኛ አማኞችም በጣም አዛኝ ነው::

تَحِيَّتُهُمۡ يَوۡمَ يَلۡقَوۡنَهُۥ سَلَٰمٞۚ وَأَعَدَّ لَهُمۡ أَجۡرٗا كَرِيمٗا

44. በሚገናኙበት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::

44. በሚገናኙበት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا

45. አንተ ነብይ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ::

45. አንተ ነብይ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ::

وَدَاعِيًا إِلَى ٱللَّهِ بِإِذۡنِهِۦ وَسِرَاجٗا مُّنِيرٗا

46. ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪና ብርሃን አድርገን ላክንህ::

46. ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪና ብርሃን አድርገን ላክንህ::

وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ بِأَنَّ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَضۡلٗا كَبِيرٗا

47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::

47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::

وَلَا تُطِعِ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَدَعۡ أَذَىٰهُمۡ وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلٗا

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንና አስመሳዮችንም አትታዘዛቸው ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው:: በአላህም ላይ ተጠጋ:: በመጠጊያነትም አላህ በቃ::

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንና አስመሳዮችንም አትታዘዛቸው ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው:: በአላህም ላይ ተጠጋ:: በመጠጊያነትም አላህ በቃ::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نَكَحۡتُمُ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ طَلَّقۡتُمُوهُنَّ مِن قَبۡلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمۡ عَلَيۡهِنَّ مِنۡ عِدَّةٖ تَعۡتَدُّونَهَاۖ فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحٗا جَمِيلٗا

49. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምዕመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም:: ሆኖም አጣቅሟቸው (ጉርሻ ስጧቸው):: መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው::

49. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምዕመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም:: ሆኖም አጣቅሟቸው (ጉርሻ ስጧቸው):: መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِنَّآ أَحۡلَلۡنَا لَكَ أَزۡوَٰجَكَ ٱلَّٰتِيٓ ءَاتَيۡتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتۡ يَمِينُكَ مِمَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَيۡكَ وَبَنَاتِ عَمِّكَ وَبَنَاتِ عَمَّٰتِكَ وَبَنَاتِ خَالِكَ وَبَنَاتِ خَٰلَٰتِكَ ٱلَّٰتِي هَاجَرۡنَ مَعَكَ وَٱمۡرَأَةٗ مُّؤۡمِنَةً إِن وَهَبَتۡ نَفۡسَهَا لِلنَّبِيِّ إِنۡ أَرَادَ ٱلنَّبِيُّ أَن يَسۡتَنكِحَهَا خَالِصَةٗ لَّكَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۗ قَدۡ عَلِمۡنَا مَا فَرَضۡنَا عَلَيۡهِمۡ فِيٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ وَمَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ لِكَيۡلَا يَكُونَ عَلَيۡكَ حَرَجٞۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

50. አንተ ነብይ ሆይ! እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፤ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም ሴቶች መካከል እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ሴቶች፤ እነዚያን ካንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎቶችህንና፤ የአክስቶችህን ሴት ልጆች (እንደዚሁም) የእናትህ ወንድም ሴት ልጆችና የእናትህ እህት ሴት ልጆች ማግባትን ላንተ ፈቅደንልሃል:: ማንኛዋም በአላህ ያመነች ሴት ራሷን ለነብዩ ብትሰጥ ነብዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ ከአማኞች ሌላ ላንተ ብቻ የተሰጠ መብት ሲሆን ፈቀድንልህ:: በአማኞች ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው ባሮች ነገር ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ አውቀናል:: ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር ያለፉትን ፈቀድንልህ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

۞ تُرۡجِي مَن تَشَآءُ مِنۡهُنَّ وَتُـٔۡوِيٓ إِلَيۡكَ مَن تَشَآءُۖ وَمَنِ ٱبۡتَغَيۡتَ مِمَّنۡ عَزَلۡتَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكَۚ ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَن تَقَرَّ أَعۡيُنُهُنَّ وَلَا يَحۡزَنَّ وَيَرۡضَيۡنَ بِمَآ ءَاتَيۡتَهُنَّ كُلُّهُنَّۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمٗا

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል የምትፈልጋትን ታቆያለህ :: የምትፈልጋትንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ:: በመፍታት ከአራቅሃትም የፈለግሃትን በመመለስ ብታስጠጋ ባንተ ላይ ኃጢአት የለብህም:: ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት ወደ አለማዘናቸዉም ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸዉም በጣም የቀረበ ነው:: አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ታጋሽ ነው::

لَّا يَحِلُّ لَكَ ٱلنِّسَآءُ مِنۢ بَعۡدُ وَلَآ أَن تَبَدَّلَ بِهِنَّ مِنۡ أَزۡوَٰجٖ وَلَوۡ أَعۡجَبَكَ حُسۡنُهُنَّ إِلَّا مَا مَلَكَتۡ يَمِينُكَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ رَّقِيبٗا

52. ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው ባሮች በስተቀር ሴቶች ላንተ አይፈቅዱልህም ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳን በእነርሱ ልትለውጥ አይፈቀድልህም። አላህ በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው::

52. ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው ባሮች በስተቀር ሴቶች ላንተ አይፈቅዱልህም ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳን በእነርሱ ልትለውጥ አይፈቀድልህም። አላህ በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَدۡخُلُواْ بُيُوتَ ٱلنَّبِيِّ إِلَّآ أَن يُؤۡذَنَ لَكُمۡ إِلَىٰ طَعَامٍ غَيۡرَ نَٰظِرِينَ إِنَىٰهُ وَلَٰكِنۡ إِذَا دُعِيتُمۡ فَٱدۡخُلُواْ فَإِذَا طَعِمۡتُمۡ فَٱنتَشِرُواْ وَلَا مُسۡتَـٔۡنِسِينَ لِحَدِيثٍۚ إِنَّ ذَٰلِكُمۡ كَانَ يُؤۡذِي ٱلنَّبِيَّ فَيَسۡتَحۡيِۦ مِنكُمۡۖ وَٱللَّهُ لَا يَسۡتَحۡيِۦ مِنَ ٱلۡحَقِّۚ وَإِذَا سَأَلۡتُمُوهُنَّ مَتَٰعٗا فَسۡـَٔلُوهُنَّ مِن وَرَآءِ حِجَابٖۚ ذَٰلِكُمۡ أَطۡهَرُ لِقُلُوبِكُمۡ وَقُلُوبِهِنَّۚ وَمَا كَانَ لَكُمۡ أَن تُؤۡذُواْ رَسُولَ ٱللَّهِ وَلَآ أَن تَنكِحُوٓاْ أَزۡوَٰجَهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦٓ أَبَدًاۚ إِنَّ ذَٰلِكُمۡ كَانَ عِندَ ٱللَّهِ عَظِيمًا

53. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መድረሱን የማትጠባበቁ ስትሆኑ ወደ ምግብ ካልተፈቀደላችሁ በስተቀር የነብዩን ቤቶች በምንም ጊዜ አትግቡ ግን በተጠራችሁ ጊዜ ግቡ በተመገባችሁም ጊዜ ወዲያውኑ ተበተኑ:: ለወግ የምትጫወቱ ሆናችሁም አትቆዩ:: ይሃችሁ ነብዩን በእርግጥ ያስቸግራል:: ከናንተም ያፍራል። ግን አላህ ከእውነት አያፍርም:: እቃንም ለመዋስ በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ሆናችሁ ጠይቋቸው። ይሃችሁ ለልቦቻችሁም ለልቦቻቸዉም የበለጠ ንጽህና ነው:: የአላህንም መልክተኛ ልታስቸግሩ ሚስቶቹንም ከእርሱ በኋላ ምንጊዜም ልታገቡ ለእናንተ አይገባችሁም። ይሃችሁ አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ነው::

إِن تُبۡدُواْ شَيۡـًٔا أَوۡ تُخۡفُوهُ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

54. ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት በእርሱ ይመነዳችኋል:: አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና::

54. ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት በእርሱ ይመነዳችኋል:: አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና::

لَّا جُنَاحَ عَلَيۡهِنَّ فِيٓ ءَابَآئِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآئِهِنَّ وَلَآ إِخۡوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآءِ إِخۡوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآءِ أَخَوَٰتِهِنَّ وَلَا نِسَآئِهِنَّ وَلَا مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُنَّۗ وَٱتَّقِينَ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدًا

55. (የነብዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸዉም፣ በወንድሞቻቸውም፣ በወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ ምዕመናት በሆኑት በሴቶቻቸዉም በጨበጧቸዉም ባሮች (አጠገብ ቢገለጡ) በእነርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለባቸዉም:: (ሴቶች ሆይ!) (ታዘዙ):: አላህን ፍሩ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡

إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِيِّۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيۡهِ وَسَلِّمُواْ تَسۡلِيمًا

56. አላህና መላዕክቱ በነብዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ:: እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ::

56. አላህና መላዕክቱ በነብዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ:: እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ::

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَأَعَدَّ لَهُمۡ عَذَابٗا مُّهِينٗا

57. እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል::

57. እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል::

وَٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ بِغَيۡرِ مَا ٱكۡتَسَبُواْ فَقَدِ ٱحۡتَمَلُواْ بُهۡتَٰنٗا وَإِثۡمٗا مُّبِينٗا

58. እነዚያም አማኞችና ምዕመናትን ባልሰሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ::

58. እነዚያም አማኞችና ምዕመናትን ባልሰሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ قُل لِّأَزۡوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ يُدۡنِينَ عَلَيۡهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّۚ ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَن يُعۡرَفۡنَ فَلَا يُؤۡذَيۡنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا

59. አንተ ነብይ ሆይ ! ለሚስቶችህ ለሴቶች ልጆችህም ለትክክለኛ አማኞች ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዳይታወቁና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

59. አንተ ነብይ ሆይ ! ለሚስቶችህ ለሴቶች ልጆችህም ለትክክለኛ አማኞች ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዳይታወቁና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

۞ لَّئِن لَّمۡ يَنتَهِ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ وَٱلۡمُرۡجِفُونَ فِي ٱلۡمَدِينَةِ لَنُغۡرِيَنَّكَ بِهِمۡ ثُمَّ لَا يُجَاوِرُونَكَ فِيهَآ إِلَّا قَلِيلٗا

60. አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ (የአመንዝራነት) በሽታ ያለባቸው በመዲናም ውስጥ (በወሬ) አሸባሪዎቹ ከዚህ ስራቸው ባይከለከሉ በእነርሱ ላይ በእርግጥ እንቀሰቅስሃለን ከዚያ በእርሷ ውስጥ ጥቂትን እንጂ አይጎራበቱህም::

60. አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ (የአመንዝራነት) በሽታ ያለባቸው በመዲናም ውስጥ (በወሬ) አሸባሪዎቹ ከዚህ ስራቸው ባይከለከሉ በእነርሱ ላይ በእርግጥ እንቀሰቅስሃለን ከዚያ በእርሷ ውስጥ ጥቂትን እንጂ አይጎራበቱህም::

مَّلۡعُونِينَۖ أَيۡنَمَا ثُقِفُوٓاْ أُخِذُواْ وَقُتِّلُواْ تَقۡتِيلٗا

61. የተረገሙ ሆነው እንጂ አይጎራበቱህም:: በየትም ስፍራ ቢገኙ ይያዛሉ:: መገደልንም ይገደላሉ::

61. የተረገሙ ሆነው እንጂ አይጎራበቱህም:: በየትም ስፍራ ቢገኙ ይያዛሉ:: መገደልንም ይገደላሉ::

سُنَّةَ ٱللَّهِ فِي ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلُۖ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّةِ ٱللَّهِ تَبۡدِيلٗا

62. እነዚህ ህጎች በእነዚያ ከዚህ በፊት ባለፉት ህዝቦች ላይ የደነገጋቸው የአላህ ድንጋጌ ናቸው:: ለአላህም ድንጋጌዎች ደግሞ ፈጽሞ መለወጥን አታገኝም::

62. እነዚህ ህጎች በእነዚያ ከዚህ በፊት ባለፉት ህዝቦች ላይ የደነገጋቸው የአላህ ድንጋጌ ናቸው:: ለአላህም ድንጋጌዎች ደግሞ ፈጽሞ መለወጥን አታገኝም::

يَسۡـَٔلُكَ ٱلنَّاسُ عَنِ ٱلسَّاعَةِۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ ٱللَّهِۚ وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ تَكُونُ قَرِيبًا

63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።» በላቸው:: የሚያሳውቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትሆን ይከጀላል::

63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።» በላቸው:: የሚያሳውቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትሆን ይከጀላል::

إِنَّ ٱللَّهَ لَعَنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَأَعَدَّ لَهُمۡ سَعِيرًا

64. አላህ ከሓዲያንን በእርግጥ ረግሟቸዋል። ለነርሱም የተጋገመችን እሳት አዘጋጅቷል::

64. አላህ ከሓዲያንን በእርግጥ ረግሟቸዋል። ለነርሱም የተጋገመችን እሳት አዘጋጅቷል::

خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ لَّا يَجِدُونَ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

65. በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም::

65. በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም::

يَوۡمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمۡ فِي ٱلنَّارِ يَقُولُونَ يَٰلَيۡتَنَآ أَطَعۡنَا ٱللَّهَ وَأَطَعۡنَا ٱلرَّسُولَا۠

66. ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ::

66. ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ::

وَقَالُواْ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعۡنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠

67. ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን መንገዱንም አሳሳቱን።

67. ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን መንገዱንም አሳሳቱን።

رَبَّنَآ ءَاتِهِمۡ ضِعۡفَيۡنِ مِنَ ٱلۡعَذَابِ وَٱلۡعَنۡهُمۡ لَعۡنٗا كَبِيرٗا

68. «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው ታላቅን እርግማንም እርገማቸው::»

68. «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው ታላቅን እርግማንም እርገማቸው::»

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ ءَاذَوۡاْ مُوسَىٰ فَبَرَّأَهُ ٱللَّهُ مِمَّا قَالُواْۚ وَكَانَ عِندَ ٱللَّهِ وَجِيهٗا

69. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው:: አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር::

69. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው:: አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር::

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَقُولُواْ قَوۡلٗا سَدِيدٗا

70. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ትክክለኛን ንግግርም ተናገሩ::

70. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ትክክለኛን ንግግርም ተናገሩ::

يُصۡلِحۡ لَكُمۡ أَعۡمَٰلَكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡۗ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدۡ فَازَ فَوۡزًا عَظِيمًا

71. ስራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ::

71. ስራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ::

إِنَّا عَرَضۡنَا ٱلۡأَمَانَةَ عَلَى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱلۡجِبَالِ فَأَبَيۡنَ أَن يَحۡمِلۡنَهَا وَأَشۡفَقۡنَ مِنۡهَا وَحَمَلَهَا ٱلۡإِنسَٰنُۖ إِنَّهُۥ كَانَ ظَلُومٗا جَهُولٗا

72. እኛ አደራን በሰማያት በምድር እና በተራራዎች ላይ አቀረብናት:: መሸከሟንም እንቢ አሉ ከእርሷም ፈሩ። ሰው ግን ተሸከማት እርሱ በጣም በደለኛና ተሳሳች ነውና::

72. እኛ አደራን በሰማያት በምድር እና በተራራዎች ላይ አቀረብናት:: መሸከሟንም እንቢ አሉ ከእርሷም ፈሩ። ሰው ግን ተሸከማት እርሱ በጣም በደለኛና ተሳሳች ነውና::

لِّيُعَذِّبَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ وَيَتُوبَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمَۢا

73. ወንዶች አስመሳዮችንና ሴቶች አስመሳዮችን ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣ በምዕምናንና በምዕመናትም ላይ አላህ ንስሃን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት):: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::

73. ወንዶች አስመሳዮችንና ሴቶች አስመሳዮችን ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣ በምዕምናንና በምዕመናትም ላይ አላህ ንስሃን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት):: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::
Footer Include