Amharic translation - Africa Academy
Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy
وَٱلنَّٰزِعَٰتِ غَرۡقٗا
1. (ነፍስን (ሩህን)) በኃይል መንጫቂዎች በሆኑት፤
وَٱلنَّٰشِطَٰتِ نَشۡطٗا
2. በቀስታ መምዘዝን መዛዦች በሆኑትም፤
وَٱلسَّٰبِحَٰتِ سَبۡحٗا
3. መዋኘትንም ዋኚዎች በሆኑት፤
فَٱلسَّٰبِقَٰتِ سَبۡقٗا
4. መቅደምንም ቀዳሚዎች በሆኑት፤
فَٱلۡمُدَبِّرَٰتِ أَمۡرٗا
5. ጉዳይንም አስተናባሪዎች በሆኑት መላዕክት እምላለሁ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)።
يَوۡمَ تَرۡجُفُ ٱلرَّاجِفَةُ
6. (ይህም የሚሆነው) ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤
تَتۡبَعُهَا ٱلرَّادِفَةُ
7. ተከታይቱም በምትከተላት ቀን (ትቀሰቀሳላችሁ)።
قُلُوبٞ يَوۡمَئِذٖ وَاجِفَةٌ
8. በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው::
أَبۡصَٰرُهَا خَٰشِعَةٞ
9. ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው።
يَقُولُونَ أَءِنَّا لَمَرۡدُودُونَ فِي ٱلۡحَافِرَةِ
10. «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ሁኔታ ተመላሾች ነን እንዴ?» ይላሉ።
أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا نَّخِرَةٗ
11. የበሰበሱ አጥንቶች በሆንን ጊዜ እንደገና እንቀሰቀሳለን?
قَالُواْ تِلۡكَ إِذٗا كَرَّةٌ خَاسِرَةٞ
12. «እንዲያማ ከሆነ ያች የኪሳራ መመለስ ናታ!» ይላሉ።
فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ
13. እርሷን (እውን የምታደርጋት) አንዲት ጩኸት ብቻ ናት።
فَإِذَا هُم بِٱلسَّاهِرَةِ
14. ወዲያውኑ በንቃት ላይ ናቸው።
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ መጣልህን?
إِذۡ نَادَىٰهُ رَبُّهُۥ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوًى
16. ጌታው በተቀደሰው ጡዋ ሸለቆ በጠራው ጊዜ፤
ٱذۡهَبۡ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
17. ወደ ፈርዖን ሂድ፤ ወሰን አልፏልና::
فَقُلۡ هَل لَّكَ إِلَىٰٓ أَن تَزَكَّىٰ
18. (እንዲህም) በለው: «እራስህን ለማጥራት ታስባለህን?
وَأَهۡدِيَكَ إِلَىٰ رَبِّكَ فَتَخۡشَىٰ
19. ጌታህንም ትፈራ ዘንድ መንገዱን ልመራህ፤ (ታስባለህን?)»
فَأَرَىٰهُ ٱلۡأٓيَةَ ٱلۡكُبۡرَىٰ
20. (ሙሳ ለፈርዖን) ታላቁንም ተዐምር አሳየው።
فَكَذَّبَ وَعَصَىٰ
21. አስተባበለም፤ አመጸም፤
ثُمَّ أَدۡبَرَ يَسۡعَىٰ
22. ከዚያ ለመጥፋት የሚተጋ ሆኖ ዞረ::
فَحَشَرَ فَنَادَىٰ
23. (ህዝቡን) ሰበሰበም ተጣራም።
فَقَالَ أَنَا۠ رَبُّكُمُ ٱلۡأَعۡلَىٰ
24. እኔ «ታላቁ ጌታችሁ ነኝ» አለም።
فَأَخَذَهُ ٱللَّهُ نَكَالَ ٱلۡأٓخِرَةِ وَٱلۡأُولَىٰٓ
25. አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ ቃል ቅጣት ያዘው::
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّمَن يَخۡشَىٰٓ
26. በዚህ ውስጥ አላህን ለሚፈሩ በእርግጥ ማስጠንቀቂያ አለበት።
ءَأَنتُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَمِ ٱلسَّمَآءُۚ بَنَىٰهَا
27. በአፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት::
رَفَعَ سَمۡكَهَا فَسَوَّىٰهَا
28. ከፍታዋን አጓነ አስተካከላትም።
وَأَغۡطَشَ لَيۡلَهَا وَأَخۡرَجَ ضُحَىٰهَا
29. ሌሊቷንም ሸፈነ፤ ቀኗንም ግልጽ አደረገ።
وَٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ ذَٰلِكَ دَحَىٰهَآ
30. ምድርንም ከዚያ በኋላ ዘረጋት።
أَخۡرَجَ مِنۡهَا مَآءَهَا وَمَرۡعَىٰهَا
31. ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ::
وَٱلۡجِبَالَ أَرۡسَىٰهَا
32. ጋራዎችንም አደላደላቸው።
مَتَٰعٗا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ
33. ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጣቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይሄን አደረገ)።
فَإِذَا جَآءَتِ ٱلطَّآمَّةُ ٱلۡكُبۡرَىٰ
34. ታላቂቱም መዓት በመጣች ጊዜ፤
يَوۡمَ يَتَذَكَّرُ ٱلۡإِنسَٰنُ مَا سَعَىٰ
35. ሰው ሁሉ የሰራውን የሚያስታውስበት ቀን፤
وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِمَن يَرَىٰ
36. ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፤
فَأَمَّا مَن طَغَىٰ
37. የካደ ሰውማ፤
وَءَاثَرَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا
38. ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፤
فَإِنَّ ٱلۡجَحِيمَ هِيَ ٱلۡمَأۡوَىٰ
39. በእርግጥ መኖሪያው ጀሀነም ናት።
وَأَمَّا مَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ وَنَهَى ٱلنَّفۡسَ عَنِ ٱلۡهَوَىٰ
40. በጌታው ፊት መቆምን የፈራና ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለማ፤
فَإِنَّ ٱلۡجَنَّةَ هِيَ ٱلۡمَأۡوَىٰ
41. በእርግጥ መኖሪያው ገነት ናት።
يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرۡسَىٰهَا
42. ስለሰዓቲቱም መነሻዋ መቼ እንደሆነ ይጠይቁሃል።
فِيمَ أَنتَ مِن ذِكۡرَىٰهَآ
43. (ለመሆኑ አንተ ስለዚያች እለት) በመወሳቷ ምን ላይ አለህበትና?
إِلَىٰ رَبِّكَ مُنتَهَىٰهَآ
44. የእርሷ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::
إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخۡشَىٰهَا
45. አንተ ያለብህ ለሚፈራት ሰው ሁሉ ስለ እርሷ (ከወዲሁ) ማስጠንቀቅ ነው።
كَأَنَّهُمۡ يَوۡمَ يَرَوۡنَهَا لَمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا عَشِيَّةً أَوۡ ضُحَىٰهَا
46. እነርሱ የሚያይዋት ቀን የአንዲትን ቀን ምሽት ወይም ረፋዷን እንጂ ያልቆዩ ይመስላሉ::
مشاركة عبر