Amharic translation - Africa Academy
Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy
إِذَا ٱلشَّمۡسُ كُوِّرَتۡ
1. ጸሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلنُّجُومُ ٱنكَدَرَتۡ
2. ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ سُيِّرَتۡ
3. ተራራዎች በተናዱ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡعِشَارُ عُطِّلَتۡ
4. የአስር ወር እርጉዝ ግመሎች ያለጠባቂ በተተው ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡوُحُوشُ حُشِرَتۡ
5. አራዊቶችም በተሰበሰቡ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ سُجِّرَتۡ
6. ባህሮችም በተቀጣጠሉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلنُّفُوسُ زُوِّجَتۡ
7. ነፍሶች በተቆራኙ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡمَوۡءُۥدَةُ سُئِلَتۡ
8. ከነሕይወቷ የተቀበረችው ሴት ልጅም በተጠየቀች ጊዜ፤
بِأَيِّ ذَنۢبٖ قُتِلَتۡ
9. በምን ወንጀል እንደተገደለች፤ በተጠየቀች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلصُّحُفُ نُشِرَتۡ
10. ጹሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ كُشِطَتۡ
11. ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجَحِيمُ سُعِّرَتۡ
12. ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡجَنَّةُ أُزۡلِفَتۡ
13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
عَلِمَتۡ نَفۡسٞ مَّآ أَحۡضَرَتۡ
14. ነፍስ (ሁሉ ከስራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلۡخُنَّسِ
15. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ተመላሾች በሆኑት (ከዋክብት) እምላለሁ::
ٱلۡجَوَارِ ٱلۡكُنَّسِ
16. አንዳንድ ጊዜ ሂያጆች በሌላ ጊዜ ገቢዎች በሆኑት
وَٱلَّيۡلِ إِذَا عَسۡعَسَ
17. በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
وَٱلصُّبۡحِ إِذَا تَنَفَّسَ
18. በንጋትም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ እምላለሁ::
إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٖ كَرِيمٖ
19. እርሱ (ቁርኣን) የተከበረው መልዕክተኛ ጅብሪል ቃል ነው።
ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي ٱلۡعَرۡشِ مَكِينٖ
20. የኃይል ባለቤት የሆነ፤ ከዙፋኑ ባለቤት ዘንድም ባለሟል የሆነ፤
مُّطَاعٖ ثَمَّ أَمِينٖ
21. በዚያ ስፍራ ትዕዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝም የሆነው (መልዕክተኛ ቃል ነው)።
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجۡنُونٖ
22. ነብያችሁም በፍጹም እብድ አይደለም።
وَلَقَدۡ رَءَاهُ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡمُبِينِ
23. በግልጹ አድማስ ላይ ሆኖ (ጅብሪልን) በእርግጥ አይቶታል።
وَمَا هُوَ عَلَى ٱلۡغَيۡبِ بِضَنِينٖ
24. እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም::
وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَيۡطَٰنٖ رَّجِيمٖ
25. (ቁርኣን) የርጉም ሰይጣን ቃልም አይደለም::
فَأَيۡنَ تَذۡهَبُونَ
26. ታዲያ (ይህንን በተመለከተ) ወዴት ትሄዳላቸሁ?
إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ
27. እርሱ የዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::
لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَسۡتَقِيمَ
28. ከናንተ መካከል ቀጥተኛ መሆንን ለፈለገ (ሁሉ መገሰጫ) ነው።
وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
29. (ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።
مشاركة عبر