Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/ro/amharic_zain

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحۡصُواْ ٱلۡعِدَّةَۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ رَبَّكُمۡۖ لَا تُخۡرِجُوهُنَّ مِنۢ بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخۡرُجۡنَ إِلَّآ أَن يَأۡتِينَ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖۚ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِۚ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَقَدۡ ظَلَمَ نَفۡسَهُۥۚ لَا تَدۡرِي لَعَلَّ ٱللَّهَ يُحۡدِثُ بَعۡدَ ذَٰلِكَ أَمۡرٗا

1. አንተ ነብይ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቷቸው፤ ዒዳንም ቁጠሩ፤ ጌታችሁን አላህን ፍሩ፤ ግልጽ የሆነችን ጠያፍ ካልሰሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጧቸው:: አይውጡም፤ ይህችም የአላህ ህግጋት ናት:: የአላህንም ህግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፤ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡

فَإِذَا بَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمۡسِكُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٍ أَوۡ فَارِقُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٖ وَأَشۡهِدُواْ ذَوَيۡ عَدۡلٖ مِّنكُمۡ وَأَقِيمُواْ ٱلشَّهَٰدَةَ لِلَّهِۚ ذَٰلِكُمۡ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّهُۥ مَخۡرَجٗا

2. ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዟቸው፤ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል::

وَيَرۡزُقۡهُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَحۡتَسِبُۚ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسۡبُهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَٰلِغُ أَمۡرِهِۦۚ قَدۡ جَعَلَ ٱللَّهُ لِكُلِّ شَيۡءٖ قَدۡرٗا

3. ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው:: አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው:: አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል::

3. ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው:: አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው:: አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል::

وَٱلَّٰٓـِٔي يَئِسۡنَ مِنَ ٱلۡمَحِيضِ مِن نِّسَآئِكُمۡ إِنِ ٱرۡتَبۡتُمۡ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَٰثَةُ أَشۡهُرٖ وَٱلَّٰٓـِٔي لَمۡ يَحِضۡنَۚ وَأُوْلَٰتُ ٱلۡأَحۡمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعۡنَ حَمۡلَهُنَّۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّهُۥ مِنۡ أَمۡرِهِۦ يُسۡرٗا

4. እነዚያም ከሴቶቻችሁ ከአደፍ (ከወር አበባ) ያቋረጡት በዒዳቸው ህግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው:: እነዚያም ገና አደፍን ያላዩ ሴቶችም ዒዳቸው እንደዚሁ ነው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል::

4. እነዚያም ከሴቶቻችሁ ከአደፍ (ከወር አበባ) ያቋረጡት በዒዳቸው ህግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው:: እነዚያም ገና አደፍን ያላዩ ሴቶችም ዒዳቸው እንደዚሁ ነው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል::

ذَٰلِكَ أَمۡرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيۡكُمۡۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يُكَفِّرۡ عَنۡهُ سَيِّـَٔاتِهِۦ وَيُعۡظِمۡ لَهُۥٓ أَجۡرًا

5. ይህ የአላህ ፍርድ ነው:: ወደ እናንተ አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ሁሉ ኃጢአቶችን ከርሱ ይሰርዝለታል:: ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል::

5. ይህ የአላህ ፍርድ ነው:: ወደ እናንተ አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ሁሉ ኃጢአቶችን ከርሱ ይሰርዝለታል:: ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል::

أَسۡكِنُوهُنَّ مِنۡ حَيۡثُ سَكَنتُم مِّن وُجۡدِكُمۡ وَلَا تُضَآرُّوهُنَّ لِتُضَيِّقُواْ عَلَيۡهِنَّۚ وَإِن كُنَّ أُوْلَٰتِ حَمۡلٖ فَأَنفِقُواْ عَلَيۡهِنَّ حَتَّىٰ يَضَعۡنَ حَمۡلَهُنَّۚ فَإِنۡ أَرۡضَعۡنَ لَكُمۡ فَـَٔاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ وَأۡتَمِرُواْ بَيۡنَكُم بِمَعۡرُوفٖۖ وَإِن تَعَاسَرۡتُمۡ فَسَتُرۡضِعُ لَهُۥٓ أُخۡرَىٰ

6. ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው:: በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ቢሆኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ። ለእናንተም ልጆቻችሁን ቢያጠቡላችሁ የልፋት ዋጋቸውን ስጧቸው:: በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፤ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች::

لِيُنفِقۡ ذُو سَعَةٖ مِّن سَعَتِهِۦۖ وَمَن قُدِرَ عَلَيۡهِ رِزۡقُهُۥ فَلۡيُنفِقۡ مِمَّآ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُۚ لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا مَآ ءَاتَىٰهَاۚ سَيَجۡعَلُ ٱللَّهُ بَعۡدَ عُسۡرٖ يُسۡرٗا

7. የችሎታ ባለቤት በችሎታው ልክ ይቀልብ፤ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይስጥ ነፍስን የሰጣትን ያህል እንጂ አያስገድድም:: አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል::

7. የችሎታ ባለቤት በችሎታው ልክ ይቀልብ፤ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይስጥ ነፍስን የሰጣትን ያህል እንጂ አያስገድድም:: አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል::

وَكَأَيِّن مِّن قَرۡيَةٍ عَتَتۡ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِۦ فَحَاسَبۡنَٰهَا حِسَابٗا شَدِيدٗا وَعَذَّبۡنَٰهَا عَذَابٗا نُّكۡرٗا

8. ከከተማም መካከል ከጌታቸው እና ከመልዕክተኞች ትዕዛዝ ያመጹ በመሆናቸው፤ ብርቱን ቁጥጥር የተቆጣጠርናቸዉና መጥፎንም ቅጣት የቀጣናቸው ብዙ ናቸው::

8. ከከተማም መካከል ከጌታቸው እና ከመልዕክተኞች ትዕዛዝ ያመጹ በመሆናቸው፤ ብርቱን ቁጥጥር የተቆጣጠርናቸዉና መጥፎንም ቅጣት የቀጣናቸው ብዙ ናቸው::

فَذَاقَتۡ وَبَالَ أَمۡرِهَا وَكَانَ عَٰقِبَةُ أَمۡرِهَا خُسۡرًا

9. የነገራቸዉንም ቅጣት ቀመሱ:: የነገራቸዉም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ::

9. የነገራቸዉንም ቅጣት ቀመሱ:: የነገራቸዉም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ::

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدٗاۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ قَدۡ أَنزَلَ ٱللَّهُ إِلَيۡكُمۡ ذِكۡرٗا

10. አላህ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እናንተም በአላህ ያመናችሁ የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደ እናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፤

10. አላህ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እናንተም በአላህ ያመናችሁ የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደ እናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፤

رَّسُولٗا يَتۡلُواْ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ مُبَيِّنَٰتٖ لِّيُخۡرِجَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَمَن يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ وَيَعۡمَلۡ صَٰلِحٗا يُدۡخِلۡهُ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ قَدۡ أَحۡسَنَ ٱللَّهُ لَهُۥ رِزۡقًا

11. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልዕክተኛን ላከ:: በአላህም አናቅጽ የሚያምን መልካምን ስራ የሚሰራም ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል አላህ ለርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ::

ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖ وَمِنَ ٱلۡأَرۡضِ مِثۡلَهُنَّۖ يَتَنَزَّلُ ٱلۡأَمۡرُ بَيۡنَهُنَّ لِتَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ قَدۡ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عِلۡمَۢا

12. አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው:: ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸዉም ትዕዛዙ ይወርዳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)::

12. አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው:: ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸዉም ትዕዛዙ ይወርዳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)::
Footer Include