Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/ro/amharic_zain

تَبَٰرَكَ ٱلَّذِي بِيَدِهِ ٱلۡمُلۡكُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

1. ያ ንግስና በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው::

ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡمَوۡتَ وَٱلۡحَيَوٰةَ لِيَبۡلُوَكُمۡ أَيُّكُمۡ أَحۡسَنُ عَمَلٗاۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفُورُ

2. ያ የየትኛችሁ ስራ ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ህይወትን የፈጠረ ነው:: እርሱም አሸናፊና መሀሪ ነው::

ٱلَّذِي خَلَقَ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖ طِبَاقٗاۖ مَّا تَرَىٰ فِي خَلۡقِ ٱلرَّحۡمَٰنِ مِن تَفَٰوُتٖۖ فَٱرۡجِعِ ٱلۡبَصَرَ هَلۡ تَرَىٰ مِن فُطُورٖ

3. ያ ሰባቱን ሰማያት የተነባበሩ ሆነው የፈጠረ ነው:: በአል ረህማን አፈጣጠርም ውስጥ ምንም ቅንጣት ያህል መዛነፍን (መቃረንና መበላሸት) አይታይም:: ዓይንህንም መልስ:: ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?

ثُمَّ ٱرۡجِعِ ٱلۡبَصَرَ كَرَّتَيۡنِ يَنقَلِبۡ إِلَيۡكَ ٱلۡبَصَرُ خَاسِئٗا وَهُوَ حَسِيرٞ

4. ከዚያም ዓይንህን መላልስ:: ዓይንህ ተዋርዶ (ተናንሶ)፤ እርሱም የደከመ ሆኖ ወደ አንተ ይመለሳል::

وَلَقَدۡ زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِمَصَٰبِيحَ وَجَعَلۡنَٰهَا رُجُومٗا لِّلشَّيَٰطِينِۖ وَأَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابَ ٱلسَّعِيرِ

5. ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት:: ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፤ ለእነርሱም ተንቀልቃይ የእሳትን ቅጣት አዘጋጀንላቸው::

وَلِلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

6. ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አላቸው:: መመላሻይቱም ገሀነም ከፋች!

إِذَآ أُلۡقُواْ فِيهَا سَمِعُواْ لَهَا شَهِيقٗا وَهِيَ تَفُورُ

7. በውስጧ በተጣሉ ጊዜ እርሷ የምትፈላ ስትሆን ከእርሷ እንደ (አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ::

تَكَادُ تَمَيَّزُ مِنَ ٱلۡغَيۡظِۖ كُلَّمَآ أُلۡقِيَ فِيهَا فَوۡجٞ سَأَلَهُمۡ خَزَنَتُهَآ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَذِيرٞ

8. ከቁጭቷ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች:: በውስጧ ቡድኖች በተጣሉ ቁጥር «ዘበኞቿ (ስለዚህ ቀን) አስፈራሪ (ነብይ) አልመጣላችሁም ነበርን?» በማለት ይጠይቋቸዋል::

قَالُواْ بَلَىٰ قَدۡ جَآءَنَا نَذِيرٞ فَكَذَّبۡنَا وَقُلۡنَا مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٍ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ كَبِيرٖ

9. «አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶልናል:: አስተባበልንም:: አላህም ምንንም አላወረደም:: እናንተ አውርዷል ስትሉ፤ በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጂ አይደላችሁም አልን» ይላሉ::

وَقَالُواْ لَوۡ كُنَّا نَسۡمَعُ أَوۡ نَعۡقِلُ مَا كُنَّا فِيٓ أَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ

10. «የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርን ኖሮ የእሳት ጓዶች ባልሆን ነበር» ይላሉ::

فَٱعۡتَرَفُواْ بِذَنۢبِهِمۡ فَسُحۡقٗا لِّأَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ

11. በኃጢአታቸዉም ያምናሉ:: ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው::

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٞ كَبِيرٞ

12. እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::

وَأَسِرُّواْ قَوۡلَكُمۡ أَوِ ٱجۡهَرُواْ بِهِۦٓۖ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

13. (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ:: ወይም በእርሱ ጩሁ:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነው::

أَلَا يَعۡلَمُ مَنۡ خَلَقَ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلۡخَبِيرُ

14. የፈጠረን አምላክ እርሱ እውቀተ ረቂቁ ውስጠ አዋቂው ሲሆን (ሚስጢርን) ሁሉ አያውቅምን?

هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ ذَلُولٗا فَٱمۡشُواْ فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُواْ مِن رِّزۡقِهِۦۖ وَإِلَيۡهِ ٱلنُّشُورُ

15. እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው:: በጋራዎቿና በመንገዶቿም ሂዱ:: ከሲሳዮም ብሉ:: (ኋላ) መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::

ءَأَمِنتُم مَّن فِي ٱلسَّمَآءِ أَن يَخۡسِفَ بِكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُ

16. በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ምድርን እንደማያሰምጥባችሁ ወዲያዉም እርሷም (እናንተኑ ውጣ) የምታረገርግ እንደማትሆን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)።

أَمۡ أَمِنتُم مَّن فِي ٱلسَّمَآءِ أَن يُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ حَاصِبٗاۖ فَسَتَعۡلَمُونَ كَيۡفَ نَذِيرِ

17. ወይስ በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ንፋስን እንደማልክባችሁ ትተማመናላችሁ? (አትፈሩም?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ

وَلَقَدۡ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ

18. እነዚያ ከእነርሱ በስተፊት የነበሩትም አስተባበሉ:: ጥላቻየም እንዴት ነበር (አስተዉል)፤

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلطَّيۡرِ فَوۡقَهُمۡ صَٰٓفَّٰتٖ وَيَقۡبِضۡنَۚ مَا يُمۡسِكُهُنَّ إِلَّا ٱلرَّحۡمَٰنُۚ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءِۭ بَصِيرٌ

19. ከበላያቸው ሰልፍ ሰርተው ወዳሉ ወፎች አይመለከቱምን? ክንፎቻቸውን ያጥፋሉ:: ከአር-ረህማን ሌላ የሚይዛቸው የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው::

أَمَّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي هُوَ جُندٞ لَّكُمۡ يَنصُرُكُم مِّن دُونِ ٱلرَّحۡمَٰنِۚ إِنِ ٱلۡكَٰفِرُونَ إِلَّا فِي غُرُورٍ

20. በእውነት ያ እርሱ ከአር-ረህማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የሆነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲያን በመታለል ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደሉም::

أَمَّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي يَرۡزُقُكُمۡ إِنۡ أَمۡسَكَ رِزۡقَهُۥۚ بَل لَّجُّواْ فِي عُتُوّٖ وَنُفُورٍ

21. ወይም ሲሳዮን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነት እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ጸኑ::

أَفَمَن يَمۡشِي مُكِبًّا عَلَىٰ وَجۡهِهِۦٓ أَهۡدَىٰٓ أَمَّن يَمۡشِي سَوِيًّا عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

22. በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚሄድ ሰው ይበልጥ የተቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚሄድ?

قُلۡ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَكُمۡ وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

23. እርሱ! ያ አላህ የፈጠራችሁ፤ ለእናተም መስሚያና ማያዎች፤ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው:: ጥቂትንም አታመሰግኑምን በላቸው::

قُلۡ هُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

24. እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናችሁ ነው:: ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ በላቸው::

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

25. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?» ይላሉ::

قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡعِلۡمُ عِندَ ٱللَّهِ وَإِنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٞ

26. እውቀቱ ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው::

فَلَمَّا رَأَوۡهُ زُلۡفَةٗ سِيٓـَٔتۡ وُجُوهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَقِيلَ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تَدَّعُونَ

27. (ቅጣቱ) ቅርብ ሆኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይከፋሉ:: ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነው ይባላሉም::

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَهۡلَكَنِيَ ٱللَّهُ وَمَن مَّعِيَ أَوۡ رَحِمَنَا فَمَن يُجِيرُ ٱلۡكَٰفِرِينَ مِنۡ عَذَابٍ أَلِيمٖ

28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁን? እስኪ ንገሩኝ? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም በማቆየት ቢያዝንልን ከሓዲያንን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው? በላቸው::

قُلۡ هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ءَامَنَّا بِهِۦ وَعَلَيۡهِ تَوَكَّلۡنَاۖ فَسَتَعۡلَمُونَ مَنۡ هُوَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ (እመኑበት የምላችሁ) አር-ረህማን ነው:: እኛ በእርሱ አመንን:: በእርሱም ላይ ተጠጋን:: ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የሆነው እርሱ ማን እንደሆነ በእርግጥ ታውቃላችሁ በላቸው::

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَصۡبَحَ مَآؤُكُمۡ غَوۡرٗا فَمَن يَأۡتِيكُم بِمَآءٖ مَّعِينِۭ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁ (እስኪንገሩኝ?) ውሃችሁ ሰራጊ ቢሆን (ወደ መሬት ቢሰርግ) ፈሳሽን (ምንጭን) ውሃ የሚያመጣላችሁ ማን ነው? በላቸው::

Footer Include