Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/ro/amharic_zain

وَٱلۡفَجۡرِ

1. በጎህ፤ እምላለሁ

1. በጎህ፤ እምላለሁ

وَلَيَالٍ عَشۡرٖ

2. በአስሩ ሌሊቶችም፤

2. በአስሩ ሌሊቶችም፤

وَٱلشَّفۡعِ وَٱلۡوَتۡرِ

3. በጥንዱም በነጠላዉም፤

3. በጥንዱም በነጠላዉም፤

وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَسۡرِ

4. በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።

4. በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።

هَلۡ فِي ذَٰلِكَ قَسَمٞ لِّذِي حِجۡرٍ

5. በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?

5. በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?

أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ

6. ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?

6. ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?

إِرَمَ ذَاتِ ٱلۡعِمَادِ

7. በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤

7. በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤

ٱلَّتِي لَمۡ يُخۡلَقۡ مِثۡلُهَا فِي ٱلۡبِلَٰدِ

8. በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤

8. በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤

وَثَمُودَ ٱلَّذِينَ جَابُواْ ٱلصَّخۡرَ بِٱلۡوَادِ

9. በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤

9. በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤

وَفِرۡعَوۡنَ ذِي ٱلۡأَوۡتَادِ

10. ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤

10. ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤

ٱلَّذِينَ طَغَوۡاْ فِي ٱلۡبِلَٰدِ

11. በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)፤

11. በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)፤

فَأَكۡثَرُواْ فِيهَا ٱلۡفَسَادَ

12. በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)

12. በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)

فَصَبَّ عَلَيۡهِمۡ رَبُّكَ سَوۡطَ عَذَابٍ

13. በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው::

13. በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው::

إِنَّ رَبَّكَ لَبِٱلۡمِرۡصَادِ

14. ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና::

14. ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና::

فَأَمَّا ٱلۡإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكۡرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَكۡرَمَنِ

15. የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባጣቀመው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል::

15. የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባጣቀመው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል::

وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيۡهِ رِزۡقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَهَٰنَنِ

16. በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል::

16. በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል::

كَلَّاۖ بَل لَّا تُكۡرِمُونَ ٱلۡيَتِيمَ

17. በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤

17. በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤

وَلَا تَحَٰٓضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ

18. ድሃንም በማብላት ላይ አትበረታቱም፤

18. ድሃንም በማብላት ላይ አትበረታቱም፤

وَتَأۡكُلُونَ ٱلتُّرَاثَ أَكۡلٗا لَّمّٗا

19. የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤

19. የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤

وَتُحِبُّونَ ٱلۡمَالَ حُبّٗا جَمّٗا

20. ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤

20. ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤

كَلَّآۖ إِذَا دُكَّتِ ٱلۡأَرۡضُ دَكّٗا دَكّٗا

21. (ሰዎች ሆይ! ተዉ):: ታቀቡ:: ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤

21. (ሰዎች ሆይ! ተዉ):: ታቀቡ:: ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤

وَجَآءَ رَبُّكَ وَٱلۡمَلَكُ صَفّٗا صَفّٗا

22. ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤

22. ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤

وَجِاْيٓءَ يَوۡمَئِذِۭ بِجَهَنَّمَۚ يَوۡمَئِذٖ يَتَذَكَّرُ ٱلۡإِنسَٰنُ وَأَنَّىٰ لَهُ ٱلذِّكۡرَىٰ

23. ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ ጥፋቱን በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?

23. ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ ጥፋቱን በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?

يَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي قَدَّمۡتُ لِحَيَاتِي

24. "ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ" ይላል።

24. "ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ" ይላል።

فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُۥٓ أَحَدٞ

25. በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።

25. በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።

وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُۥٓ أَحَدٞ

26. የእርሱንም፤አሰተሳሰር አንድም አካል አያስርም::

26. የእርሱንም፤አሰተሳሰር አንድም አካል አያስርም::

يَٰٓأَيَّتُهَا ٱلنَّفۡسُ ٱلۡمُطۡمَئِنَّةُ

27. (ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ በአላህ የረካሺው ነፍስ ሆይ!

27. (ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ በአላህ የረካሺው ነፍስ ሆይ!

ٱرۡجِعِيٓ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةٗ مَّرۡضِيَّةٗ

28. (ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ::

28. (ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ::

فَٱدۡخُلِي فِي عِبَٰدِي

29. ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ::

29. ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ::

وَٱدۡخُلِي جَنَّتِي

30. ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች::

30. ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች::
Footer Include