Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/aa/amharic_zain

عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ

1. ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

1. ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ

2. ከታላቁ ዜና (ቁርኣን) ይጠያየቃሉ።

2. ከታላቁ ዜና (ቁርኣን) ይጠያየቃሉ።

ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ

3. ስለዚያ እነርሱ በእርሱ ላይ ስለተለያዩበት (ስለተወዛገቡበት)::

3. ስለዚያ እነርሱ በእርሱ ላይ ስለተለያዩበት (ስለተወዛገቡበት)::

كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ

4. ጉዳዩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ::

4. ጉዳዩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ::

ثُمَّ كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ

5. ከዚያም ይከልከሉ፤ (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ።

5. ከዚያም ይከልከሉ፤ (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ።

أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدٗا

6. ምድርን ምንጣፍ አላደርግንምን?

6. ምድርን ምንጣፍ አላደርግንምን?

وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادٗا

7. ጋራዎችንም ችካሎች (አላደረግንምን)?

7. ጋራዎችንም ችካሎች (አላደረግንምን)?

وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجٗا

8. ጥንዶች አድርገንም ፈጠርናችሁ።

8. ጥንዶች አድርገንም ፈጠርናችሁ።

وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتٗا

9. እንቅልፋችሁንም እረፍት አደረግን።

9. እንቅልፋችሁንም እረፍት አደረግን።

وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسٗا

10. ሌሊቱንም ልባስ አደረግን::

10. ሌሊቱንም ልባስ አደረግን::

وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشٗا

11. ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ (ለጉዳይ መከወኛ) አደረግን።

11. ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ (ለጉዳይ መከወኛ) አደረግን።

وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعٗا شِدَادٗا

12. ከበላያቸሁም ሰባት ብርቱዎችን (ሰማያት) ገነባን።

12. ከበላያቸሁም ሰባት ብርቱዎችን (ሰማያት) ገነባን።

وَجَعَلۡنَا سِرَاجٗا وَهَّاجٗا

13. አንጸባራቂ ብርሃንንም አደርግንላችሁ።

13. አንጸባራቂ ብርሃንንም አደርግንላችሁ።

وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءٗ ثَجَّاجٗا

14. ከአረገዙት ደመናዎችም የሚንቧቧ ውሃን አወረድን::

14. ከአረገዙት ደመናዎችም የሚንቧቧ ውሃን አወረድን::

لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبّٗا وَنَبَاتٗا

15.በእርሱ እህልንና ቅጠላ ቅጠልን፤ እናወጣ ዘንድ(አወረድን)።

15.በእርሱ እህልንና ቅጠላ ቅጠልን፤ እናወጣ ዘንድ(አወረድን)።

وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا

16. የተቆላለፉ አትክልቶችንም ::

16. የተቆላለፉ አትክልቶችንም ::

إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتٗا

17. (በህዝቦች መካከልም) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው።

17. (በህዝቦች መካከልም) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው።

يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجٗا

18. (ይሀዉም) በቀንዱ በሚነፋበትና በቡድን በቡድን ሆናችሁም በምትመጡበት ቀን ነው።

18. (ይሀዉም) በቀንዱ በሚነፋበትና በቡድን በቡድን ሆናችሁም በምትመጡበት ቀን ነው።

وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبٗا

19. ሰማይም በምትከፈትና ባለ ብዙ ደጃፎችም በምትሆንበት ቀን፤

19. ሰማይም በምትከፈትና ባለ ብዙ ደጃፎችም በምትሆንበት ቀን፤

وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا

20. ጋራዎችም በሚናዱበትና እንደ ሲሪብዶም በሚሆንበትም ቀን ነው።

20. ጋራዎችም በሚናዱበትና እንደ ሲሪብዶም በሚሆንበትም ቀን ነው።

إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادٗا

21. ገሀነም (ለከሓዲያን) መጠባበቂያ ኬላ (ስፍራ) ናት::

21. ገሀነም (ለከሓዲያን) መጠባበቂያ ኬላ (ስፍራ) ናት::

لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابٗا

22. ለህግ ተላላፊዎች መመላለሻ ስትሆን።

22. ለህግ ተላላፊዎች መመላለሻ ስትሆን።

لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابٗا

23. በውስጧ ብዙ ዘመናትን ነዋሪዎች ሲሆኑ፤

23. በውስጧ ብዙ ዘመናትን ነዋሪዎች ሲሆኑ፤

لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدٗا وَلَا شَرَابًا

24. በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጠንም አይቀምሱም (አያገኙም)።

24. በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጠንም አይቀምሱም (አያገኙም)።

إِلَّا حَمِيمٗا وَغَسَّاقٗا

25. ሙቅ የፈላ ውሃንና እዥን እንጂ

25. ሙቅ የፈላ ውሃንና እዥን እንጂ

جَزَآءٗ وِفَاقًا

26. ተመጣጣኝን ምንዳ ይመነዳሉ።

26. ተመጣጣኝን ምንዳ ይመነዳሉ።

إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابٗا

27. ምርመራ (እንዳለባቸው) ቅንጣት አይጠብቁም ነበርና።

27. ምርመራ (እንዳለባቸው) ቅንጣት አይጠብቁም ነበርና።

وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابٗا

28. በአናቅጻችንም ማስተባበልን አስተባበሉ።

28. በአናቅጻችንም ማስተባበልን አስተባበሉ።

وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبٗا

29. ነገሩን ሁሉ የተፃፈ ሲሆን አጠቃለልነው።

29. ነገሩን ሁሉ የተፃፈ ሲሆን አጠቃለልነው።

فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا

30. «(የጃችሁን) ቅመሱም፤ ቅጣትን እንጂ ሌላን አንጨምርላችሁም» (ይባላሉም)።

30. «(የጃችሁን) ቅመሱም፤ ቅጣትን እንጂ ሌላን አንጨምርላችሁም» (ይባላሉም)።

إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا

31. ለጥንቅቆቹ (አላህን ለሚፈሩ) ስኬት አላቸው።

31. ለጥንቅቆቹ (አላህን ለሚፈሩ) ስኬት አላቸው።

حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبٗا

32. አትክልቶችና ወይኖችም፤

32. አትክልቶችና ወይኖችም፤

وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابٗا

33. በእድሜ እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉችማዎችም፤

33. በእድሜ እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉችማዎችም፤

وَكَأۡسٗا دِهَاقٗا

34. የተሞሉ ብርጭቆዎችም፤

34. የተሞሉ ብርጭቆዎችም፤

لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا كِذَّٰبٗا

35. በውስጧ ትርፍ ቃልንም፤ ማስዋሸትንም አይሰሙም::

35. በውስጧ ትርፍ ቃልንም፤ ማስዋሸትንም አይሰሙም::

جَزَآءٗ مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابٗا

36. ከጌታህ የሆነን ምንዳ፤ በቂ ስጦታን ተሰጡ::

36. ከጌታህ የሆነን ምንዳ፤ በቂ ስጦታን ተሰጡ::

رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابٗا

37. የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ላለው ሁሉ ጌታ ከሆነውና በጣም አዛኝ ከሆነው ተመነዱ፤ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም::

37. የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ላለው ሁሉ ጌታ ከሆነውና በጣም አዛኝ ከሆነው ተመነዱ፤ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም::

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفّٗاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابٗا

38. መልአኩ (ጅብሪል) እና ሌሎች መላዕክትም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙበት ቀን አረህማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ብቻ ቢሆን እንጂ መነጋገርን አይችሉም።

38. መልአኩ (ጅብሪል) እና ሌሎች መላዕክትም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙበት ቀን አረህማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ብቻ ቢሆን እንጂ መነጋገርን አይችሉም።

ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا

39. ያ! የእውነት ቀን ነው። የፈለገ ሰው ወደ ጌታው በመልካም ተግባር መመለስን ተግባሩ አድርጎ ይይዛል።

39. ያ! የእውነት ቀን ነው። የፈለገ ሰው ወደ ጌታው በመልካም ተግባር መመለስን ተግባሩ አድርጎ ይይዛል።

إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابٗا قَرِيبٗا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا

40. እኛ ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ። ሰዎች ሁሉ በሁለት እጆቻቸው ያስቀደሙትን በግልጽ የሚያይበትና ከሓዲያን ሁሉ «ዋ ምኞቴ! ምንነው አፈር በሆንኩ ባልተቀሰቀስኩኝ» የሚሉበት ቀን።

40. እኛ ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ። ሰዎች ሁሉ በሁለት እጆቻቸው ያስቀደሙትን በግልጽ የሚያይበትና ከሓዲያን ሁሉ «ዋ ምኞቴ! ምንነው አፈር በሆንኩ ባልተቀሰቀስኩኝ» የሚሉበት ቀን።
Footer Include