Header Include

Amharic translation - Africa Academy

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

QR Code https://quran.islamcontent.com/aa/amharic_zain

وَيۡلٞ لِّلۡمُطَفِّفِينَ

1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤

1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤

ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ

2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤

2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤

وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ

3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት)::

3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት)::

أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ

4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን?

4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን?

لِيَوۡمٍ عَظِيمٖ

5. ለታላቁ ቀን፤

5. ለታላቁ ቀን፤

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን)::

6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን)::

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٖ

7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ"ሲጂን" ውስጥ ነው።

7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ"ሲጂን" ውስጥ ነው።

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينٞ

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ሲጂን" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ሲጂን" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ

10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።

10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።

ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት::

11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት::

وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ

12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም::

12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም::

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል::

13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል::

كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው::

14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው::

كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّمَحۡجُوبُونَ

15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው::

15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው::

ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ

16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው::

16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው::

ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ

17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ::

17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ::

كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ"ዒሊዩን" ውስጥ ነው።

18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ"ዒሊዩን" ውስጥ ነው።

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ

19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ዒሊዩን"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ዒሊዩን"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ

20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።

يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ

21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)።

21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)።

إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ

22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ።

23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ።

تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ

24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)።

24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)።

يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقٖ مَّخۡتُومٍ

25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ::

25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ::

خِتَٰمُهُۥ مِسۡكٞۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ

26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ።

26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ።

وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ

27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው።

27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው።

عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ

28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት።

28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት።

إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ

29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር።

29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር።

وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ

30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር::

30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር::

وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ

31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር።

31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር።

وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ

32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- "እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።" ይሉ ነበር።

32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- "እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።" ይሉ ነበር።

وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ

33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ::

33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ::

فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ

34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ::

34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ::

عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ

35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)።

35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)።

هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)::

36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)::
Footer Include